“ ምኒልክ ማነው ? ”
(የአንድ ተቋም ሰልጣኞች ጥያቄ)
በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ የጋዜጠኝነት ስልጠና የሚሰጥ ተቋም
አለ፡፡ አሰልጣኙ ስለ ቃለ መጠይቅ (ቃለ ምልልስ) እያስተማሩ የተለያዩ ምሳሌዎች እያቀረቡ ያስረዳሉ፡፡ በመካከል ‹‹ ለመሆኑ
አፄ ምኒልክ የት ተወለዱ? ›› ብለው ጠየቁ ለተግባር ልምምድ መድረክ ላይ ለነበሩት ሰልጣኞች ቡድን ውስጥ መልስ የሚሰጥ
አልተገኘም፤ ከ35 በላይ ለሆኑኑት በክፍሉ ውስጥ ለሚገኙት ጥያቄውን ደገሙት ወዲያው ‹‹ የቤት ስራ ይሁን›› ብለው ወጡ፡፡
ከ3 ቀናት በኃላ ገና እንደገቡ ሁለት ሰልጣኞች እጅ አወጡ ‹‹ ሳይቀድሙን…….. ›› ብለው ያሰቡ ይመስላል፡፡ ለአንዱ ዕድል
ሰጡ ‹‹ ለመሆኑ ምኒልክ ማነው ? ›› ብሎ የቤት ስራ የነበረው ለመምህሩ የክፍል ስራ አድርጎ ጠየቀ ፡፡ መምህሩም እየተገረሙ
ወደ አንደኛው እጅ አውጥቶ ወደነበረው ‹‹አንተስ መልስ ነው
? ›› አሉት፡፡ ‹‹ አይደለም የእኔም ጥያቄ ይሄው ነበር ›› አለና አረፈው፡፡
#መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ; ይባላል በጎ ነው፡፡ ግን ስለ አፄ ምኒልክ
ጽሑፍ@ ነጋሪ@ ….. ጠፍቶ ይሆን? እውነት ግን የአሁን ዘመን ወገኖች አብዛኞቻችን ስለ ቀደምት የኢትዮጵያ ባለውለታዎች
እናውቅ ይሆን? ታዲያ ለልጆቻችንስ ማን አስረዳቸው ?ለማንኛውም ከተረዳሁት ጥቂቱን ልመስክር ፡፡