ነገረ ሃይማኖት

ሃይማኖት ማለት 'አምነ' አመነ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን እምነት ማለት ነው።ከዚሁ ግስም ሃይማኖት
የሚል ስም ይወጣል። ሃይማኖት ማለትም ማመን ፤ መታመን ማለት ነው። አንዳንድ ሊቃውንት ሃይምነ ፤
አሚን ከሚል ግስ የተገኘ መሆኑንም ይናገራሉ።
በአጠቃላይ ሃይማኖት ማለት ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ እግዚአብሔር አለ ብሎ ማመን እና ለቃሉም መታመን (መገዛት) ነው።
 
የሃይማኖት የትመጣ፦
ዘመን የማይቆጠርለት እግዚአብሔር ክብሩን ሊያካፍል ፍጥረታትን ሲፈጥር በጀመጀመሪያው ዕትና ሰዓት
በሰማይ መላእክትን ሲፈጥር በሥራው መገለጡ የሃይማኖት መሠረት ነው። በመቀጠልም በዕለተ ግርብ ሰውን
ፈጥሮ የሕይወት እስትንፋስ እፍ ሲልበት በመንፈሱ አማካኝነት ሃይማኖትን ወይም እግዚአብሄርን ማመንን
አምሮ ሠጥቶታል። ዘፍ 1፥1 (26) (2-7)
ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔር ሃይማኖትን (የማመን) ፍላጎትን በውስጣችን እንዳስቀመጠና ይኸውም የእርሱ
ስጦታ መሆኑን አስረድቷል። ''እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳችም እንደሚጎድለው
በሰው እጅ አይገለገልም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ እግዚአብሔርን ይፈለጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን
ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ . . . . ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም'' ሐዋ17፥25-27
አምላካችን እግዚአብሔር ጻድቁ ኢዮብን ባነጋገረበት ቅዱስ ቃሉ ''በውስጡስ ጥበብን ያኖረ ፤ ለሰውልብ
ማስተዋልን የሰጠ ማነው?'' በማለት ሰው በልቡ በሚገኝ ጥበብና ማስተዋል ወይም ''እምነት'' የተነሣ ከፈጣሪው
ጋር እንደሚገናኝ ገልጾአል። ኢዮ 38፥36
አምላክ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን የማያምኑ ወገኖች እንኳን በባእድ ነገሮች ፤ በራሳቸው ፤ በገንዘብ. እና በመሳሰሉት ሊመኩ መምከራቸው የሚያስረዳው ሰው ረዳት ፈላጊ የመሆን ዝንባሌ በተፈጥሮው እንዳለ ሲሆን
ይህም ሊታመን የሚገባው እውነተኛ አምላክ መኖሩን ያመለክታል። ምክንያቱም በአንዳች ነገር ሳያምን ወይም
ሳይመካ የሚኖር ሰው የለምና አንድ ሰው አላምንም እንኳን ቢል አለማመኑ በራሱ ለርሱ ሃይማኖት ወይም
በአስተሳሰቡ መመካት ይሆንበታል።
አንዳንድ ለፍልስፍና እና ለፖለቲካ መንገድ ከፈትን ያሉ ፈላስፎች ፀረ-ሃይማኖት አመለካከትን በዓለማችን
መዝራታቸውን ይታወቃል። ለምሳሌ (ከ1818-1883) የኖረው ካርል ማርክስ ሃይማኖት ማኅበረሰብን መቆጣጠሪያ
መሳሪያ እንደሆነ ግምቱን አስፋፍቶ ነበር። ጀርመናዊው ኒቼ (ፍሬድሪከ ኒቼ) በ1844
'ሃይማኖት ሰውን ባሪያ ማድረጊያ ነው' በማለት ተፈላሰፍኩ ያለ ነበር ራሱን ፀረ-ክርስቶስ ብሎ የሚጠራው ኒቼ
እንኳንስ በፍልስፍናው እግዚአብሔርን ሊያውቅ ፤ የራሱን ችግር ማወቅ ተስኖት አምሮውን አጥቶ መሞቱ መሞቱ
ይታወቃል ሃይማኖትን ተቃውሞ ፖለቲካን አስፋፋለሁ ያለው ካርል ማርከስ የፈጠረው ርዕዮተ ዓለም ለብዙዎች
እልዊት እንጂ መፍትሔ አለሆነም የሃይማኖት ተቃዋሚዎች ብዙዎቹ እግዚአብሔር የለም ቢሉም የሠይጣንን መኖር
ግን አረጋግጠዋል። በዘመናችንም የግብር ልጆቹ በእግዚአብሔር ሳያምኑ ነገር ግን የክፉ መንፈስን መኖር ፤ ሰዎች
በምትሀቱ መያዙን የሚያመለክቱ መጽሐፎችና ፊልሞቻቸው ምስክር ናቸው።
ሃይማኖት ''እግዚአብሔር አለ'' ብለው ከልብ የሚቀበሉት (የሚያረጋግጡት) ነው። ምክንየቱም ብዙ ነገሮችን
በስሜት ሕዋሳት እና በዕውቀት እናረጋግጣለን እግዚአብሔር ግን ከስሜት እና ከአእምሮ በላይ በመሆኑ 'አለ ፤
ሁሉን ያደርጋል ፤ የሚሳነው ነገር የለም ፤ . . . 'ብሎ እውነትን በማረጋገጥ መቀበል ብቻ ነው።
ለአእምሮ ወሰን ሲኖረው ለእግዚአብሔር ግን ወሰን የለውም። ስለዚህ ሰው የማይችለውን ነገር ሊያደርግ ቢፈልግ
አይችልም እና መቀበል ይኖርበታለ። ''ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ ለእያንዳንዱ እመክራለሁ . . . ''
ሮሜ 12፥3 ዮሐ 4፥24
በአጠቃላይ ዓለማችን ስለ ሃየማኖት የተለያዩ አመለካከቶችን ብታስተናግድም እኛ ግን አበው እንደ አስተማሩን ፤
ቅዱሳት መጻሕፍትም እንዳረጋገጡልን። ሃይማኖት በእግዚአብሔር እና በመላእክት እንደዚሁም እግዚአብሔር አዳምና
ሔዋንን ፈጥሮ ከማነጋገሩ ጀምሮ እንደተገለጠልን (እንደሰጠን) እናምናለን። ''ሁሉ በርሱ ሆነ. . .'ዮሐ.1፥13
ሃይማኖት ማለት 'አምነ' አመነ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን እምነት ማለት ነው።ከዚሁ ግስም ሃይማኖት
የሚል ስም ይወጣል። ሃይማኖት ማለትም ማመን ፤ መታመን ማለት ነው። አንዳንድ ሊቃውንት ሃይምነ ፤
አሚን ከሚል ግስ የተገኘ መሆኑንም ይናገራሉ።
በአጠቃላይ ሃይማኖት ማለት ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ እግዚአብሔር አለ ብሎ ማመን እና ለቃሉም መታመን (መገዛት) ነው።

No comments:

Post a Comment