“እየሩሳሌምን
በልባችሁ አስቡ” ‹‹ት.ኤር 51÷51››
ነቢዩ ኤርምያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ539 ዓ/ዓለም ገደማ ስለኢየሩሳሌም ነፃ መውጣት እና
ስለ ባቢሎን መፍረስ የተናገረው ነው፡፡ ፍፃሜውም በኢየሩሳሌም ስለሚፈጸመው ነገረድኅነት እና ከክርስቲያኖች ልብ የማትጠፋ ሀገር
ስለመሆኗ የሚያመለክት ነው፡፡
እስራኤል
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ለይስሐቅ ልጅ ለያዕቆብ የሰጠው ስያሜ ነው፣ ካልባረከኝ አልለቅምህ
ብሎ ነበርና “ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፋል” ሲል እስራኤል አለው፡፡ ዘፍ. 32÷22 በኋላም የያዕቆብ ልጆች
የተጠሩበት እና ከሰሎሞን በኋላ ዐሥሩ ነገዶች ያቋቋሙት የሰሜናዊው ግዛት (መንግሥት) ስያሜ ሆኗል፡፡ ዘፍ 49÷7 ዘዳ
14÷39 1ኛ ነገ.12÷16
በአዲስ ኪዳን የክርስቶስ ተከታዮች እስራኤል ዘነፍስ ተብለዋል ሮሜ. 9 ገላ. 3÷6
ሮሜ. 4÷12
እየሩሳሌም
ኢየሩሳሌም ማለት መሠረት ሠላም፣ ሀገረ ሠላም፣ የሠላም ምልክት…. ማለት ነው፡፡ ስትጠራም
የእግዚአብሔር ከተማ፣ ቅድስት ከተማ፣ የዳዊት ከተማ ተብላ በቅዱሳት መጻሕፍት ተጠቅሳለች ንጉሠ ሰላም የተባለው የጌታችን ምሳሌ
ሆኖ የሚነገረው መልከፄዴክ እንደመሠረታት ይነገራል፡፡ ዘፍ. 14÷ ነህ. 11÷1 የአበ ብዙኃን አብርሃም የልጆቹ፣ የበርካታ
ነቢያት ሀገራቸው ፣ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ዳዊትም ከኢያቡሳውያን ማርኮ ከተማው ያደረጋት በመሆኗ የነቢያት ትንቢት ፍፃሜ አግኝቶ
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከልደት እስከ ዕርገት የኖረባት፣ ሐዋርያት የተጠሩባት፣ ነገረድኅነት የተፈፀመባት በመሆኗ
በእውነትም ቅድስት ሀገር ናት፣ በማዕከለ ኢየሩሳሌም ጽርሐጽዮን የሰሎሞን ቤተመቅደስ፣ ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ቀራንዮ መከራ
መስቀል የተቀበለባቸው ቦታዎች ይገኛሉ፡፡