Friday 12 July 2013

ሐዋርያት



ሐዋርያ የሚለው ስያሜ ሖረ፣ሔደ ከሚለው ከግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙ የተላከ፣ሒያጅ፣ልዑክ ማለት ነው፡፡ ይህ መጠሪያ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተማር ዘመኑ ከተለያዩ ተግባራት እንዲከተሉት ከጠራቸው ለ12 ደቀ መዛሙርት የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ማር 3÷13 በኃላም ወንጌልን እንዲሰብኩ “ሑሩ ወመሐሩ” ብሏቸዋልና ሐዋርያት ተባሉ፡፡ ማቴ 28÷19 ቅዱሳን ሐዋርያትም ከድሆች፣ ከሀብታሞች፣ ከምሁራን፣ ካልተማሩ ወገኖች ሲመርጥ ለዓለምም ክብር እንዲያጎናጽፉ የበረከት መልዕክተኞች የዓለም ጌጦች አድርጓቸዋል፡፡



የሐዋርያት ነገድ እና በዓላት
የሐዋርያው ስም                   ነገድ                    በዓላት

1.   ቅዱስ ጴጥሮስ                   ነገደ ሮቤል                ሐምሌ 5
2.   ቅዱስ እንድርያስ                 ነገደ ሮቤል                ታህሳስ 4
3.   ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ      ነገደ ሌዊ                 ሚያዚያ 17
4.   ቅዱስ ዮሐንስ                    ነገደ ይሁዳ                ጥር 4
5.   ቅዱስ ፊሊጶስ                    ነገደ ዛብሎን               ህዳር 22
6.   ቅዱስ በርተሎሜዎስ              ነገደ ንፍታሌም            መስከረም 1
7.   ቅዱስ ማቴዎስ                   ነገደ ይሳኮር               ጥቅምት 12
8.   ቅዱስ ቶማስ                    ነገደ አሴር                   ሰኔ 6
9.   ቅድስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ       ነገደ ጋድ                 የካቲት 8
10. ቅዱስ ታዲዎስ                   ነገደ ዮሴፍ                ሐምሌ 2
11. ቅዱስ ናትናኤል                  ነገደ ብንያም               ሐምሌ 10
12. ቅዱስ ማትያስ                   ነገደ ዳን                  መጋቢት 8




የሐዋርያት አገልግሎት በምድረ እስራኤል ቢጀመርም ዓለምን ዞረው አስተምረዋል ጌታችንን በዓይናቸው ያዩ በጆሮአቸው የሰሙ በእጃቸው የዳሰሱት ከመሆናቸው የመጀመሪያና እውነተኛ ምስክሮ ሆነዋል፡፡ 1ኛዮሐ1÷1-3

ቅዱስ ጳውሎስ ከሐዋርያት በኃላ ቢጠራም ጌታችን በደማስቆ የተገለጸለት በጌታችን የተሾመና ቅዱስ ሆኖ በመገኘቱ ሐዋርያ ይባላል፡፡ ሮሜ 1÷1 ገላ 1÷1-2 ሐዋ 9

ሐዋርያት የቤተክርስቲያን መሪዎችና የክህነት አብነቶች ናቸው፡፡ ዮሐ 20÷23 ኤፌ 2÷20 ማቴ 16÷18 ሃይማኖት የስነምግባር ትምህርት በሐዋርያት በኩል ለቤተክርስቲያን ተሰጥቷል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት እስከ ሞት በምስክርነት ጸንተው በሰማዕትነት አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ጌታችንም የአማላጅነት ክብርን ሾሟቸዋል እነሆ በአጸደ ነፍስ ሆነው ያማልዳሉ፡፡  ማቴ19÷19-24

የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት አይለየን አሜን!
 


No comments:

Post a Comment